Seattle Public Schools

Student Family Portal

የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበጀት ማሻሻያ እና ቀጣይ እርምጃዎች

የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበጀት ማሻሻያ እና ቀጣይ እርምጃዎች

ውድ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች፣ሰራተኞች እና ማህበረሰብ፣

ለተማሪዎቻችን እና ለት/ቤቶቻችን ያላሰለሰ ጥረት ስላደረጉልን እናመሰግናለን።እነዚህን ፈታኝ ጊዜዎች ለማለፍ ስንዳስስ ለምታደርጉልን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።

በተለይ ከፍተኛ ጉድለት ስላጋጠመን በጀታችንን ማመጣጠን ቀላል ስራ አይደለም።ሆኖም፣የመመሪያ ተልእኳችን ግልጽ ሆኖ ይቆያል፡እያንዳንዱ ተማሪ ትምህርት እና እድገትን በሚያበረታታ አካባቢ ጥራት ያለው ትምህርት ማግኘቱን ማረጋገጥ።

የበጀት ተግዳሮት

በስቴቱ እና በሀገሪቱ ውስጥ እንዳሉት ብዙ ዲስትሪክቶችች፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቀጣይነት ካለው የበጀት እጥረት በመታገል ላይ ነው።የተማሪዎች ምዝገባ ማሽቆልቆል — የመኖሪያ ቤት ወጪ መጨመር፣የኮቪድ ቀጣይነት ያለው ተጽእኖ፣እና ወደ ቤት-ተኮር ትምህርት እና የግል ትምህርት ቤቶች በተደረገው ሽግግር ጉዳዩን አባብሶታል። በተጨማሪም፣የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የስቴት ፈንድ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል።

በጣም ወሳኝ በሆነ የፋይናንስ ወቅት ላይ እናገኛለን።ሆኖም እነዚህ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የላቀ ደረጃ ላይ የሚደርሱበት ቦታ ሆነው ይቆያሉ።ወደ 50,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን በኩራት እናገለግላለን፣የበለጸጉ አካዴሚያዊ ልምዶች፣ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች፣እና አስፈላጊ የልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎቶችን እናቀባለን።ግባችን እነዚህን እድሎች ለመጠበቅ እና እያንዳንዱ ተማሪ፣በትምህርት ቤቱ፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝ እና እንዲያድግ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ማረጋገጥ ነው።

ቀጣዩ ጉዛችን

እነዚህ አስቸጋሪ ውሳኔዎችን ስንወስን ብዙዎቻችሁ እንደተጨነቃቹ እናውቃለን፣እና ስለእርስዎ ፍላጎት እና አስተያየት እናመሰግናለን።ለ2025-26 የትምህርት ዘመን የ94 ሚሊዮን ዶላር እጥረት አጋጥሞናል።ይህንን ለመፍታት በርካታ ስልቶችን እየተከተልን ነው:

1. የትምህርት ቤቶች ማዋሃድ: በጥንቃቄ ከተመለከትን እና ስጋቶችዎን ካዳመጥን በኋላ በ2025-26 የትምህርት ዘመን አራት ትምህርት ቤቶችን ለማዋሃድ አቅደናል።

ይህ ማዋሃድ ፋይናንሳችንን ለማረጋጋት ትልቅ የስትራቴጂ አካል ነው።እነዚህን አራት በቂ ተማሪዎች የሌሉዋቸው ትምህርት ቤቶች በመዝጋት የበለጠ ጠንካራና ዘላቂ የሆነ የትምህርት ሥርዓት መገንባት እንጀምራለን።ዲስትሪክታችን ለተማሪዎቻችን የሚገባውን ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት መስጠቱን ለማረጋገጥ ይህ የተሻለው የወደፊት መንገድ ነው።

ለትምህርት ቦርድ የማቀርበው የመጀመሪያ ምክር የሚከተለው ይሆናል፡

  • ሰሜን ምዕራብ ክልል: North Beach አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ከViewlands አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማዋሃድ
  • ሰሜን ምስራቅ ክልል: Sacajawea አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ከ John Rogers አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማዋሃድ
  • መካከለኛው ክልል: Stevens አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ከMontlake አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማዋሃድ
  • ደቡብ ምዕራብ ክልል: Sanislo አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተዘግቶ ከHighland Park አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማዋሃድ

ይህ ለውጥ አስቸጋሪ እንደሆነ እንረዳለን።እነዚህን ትምህርት ቤቶች የመረጥናቸው እንደ የግንባታቸው ሁኔታ፣ቦታ እና በተማሪዎች እና ቤተሰቦች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን የመቀነስ ግብ ላይ በመመስረት ነው።የሽግ ግር ቡድኑ በዚሁ ከተሳተፉት ማህበረሰቦች ጋር አብሮ በመስራት ምቹ እና ደጋፊ የሆነ ሂደትን እንዲኖራቸው ያረጋግጣል።

ማህበረሰባችን ከትምህርት ቤቶቹ ጋር ያለውን ጥልቅ ግንኙነት እንገነዘባለን እና ሂደቱ ግልፅ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን። ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ፣ተፅዕኖ በደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች የተሳትፎ ስብሰባዎችን እናካሂዳለን፣በየሳምንቱ በአካል እስከ ህዳር 23 ድረስ በአካል ድጋፍ እንሰጣለን።በተጨማሪም፣በዲስትሪክቲ ደረጃ የመረጃ ስብሰባ ሐሙስ ህዳር 14፣ከ 6:30 እስከ 7:30 p.m.ይካሄዳል።

2. ለህግ አውጭ ድጋፍ መጠየቅ: የበጀት እጥረታችንን ለመሸፈን በተለይም እንደ የልዩ ፍላጎት ትምህርት፣መጓጓዣ እና የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ከየስቴቱ ህግ አውጪዎች ሙሉ ድጋፍን እንሻለን።በተጨማሪም፣ የኢንተርፈንድን ብድር እንዲራዘምልን እና የግብር ስልጣናችንን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም እንፈልጋለን።

3. የማዕከላዊ ቢሮ ቅነሳዎች: ከመማሪያ ክፍሎች መዝጋት ለማስቀረት፣የሰራተኞች መልሶ ማደራጀትን እና ማስተካከያዎችን ጨምሮ በማእከላዊ ጽህፈት ቤታችን ውስጥ ያሉ ሊቀነሱ የሚችሉ ስራ ዎችን እየለየን ነው።

4. የትምህርት ቤት ደወል ጊዜ መቀየር: ወደ ሶስት-ደረጃ የደወል መርሃ ግብር እንሸጋገራለን፣ይህም ብዙ የአውቶቡስ መስመሮችን በትንሽ አውቶቡሶች በመሸፈን ወጪን ለመቀነስ ያስችለናል።

5. Levies(ግብር)ማደስ: በየካቲት 2025 መራጮች ሁለት ወሳኝ ግብሮችን እንዲያሳድሱ እንጠይቃለን – የትምህርት ፕሮግራሞች እና ኦፕሬሽኖች (EP&O) Levy እና የሕንፃ ልቀት (BEX VI) ሌቪ – ለት / ቤት ስራዎች እና ጥገና አስፈላጊ የገንዘብ ድጋፍ።

የተማሪዎች ምዝገባ ለመጨመር የሚደረጉ ጥረቶች

ብዙ ቤተሰቦችን ወደ ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ለመሳብ የተማሪዎች የምዝገባ ጥናት እያደረግን ነው።ይህ ጥናት እስከ ታህሳስ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፣ይህም የምልመላ እና የማቆየት ጥረታችንን ይመራናል እንዲሁም ጠንካራ፣የበለጠ ንቁ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ እንድንገነባ ይረዳናል።

ቀጣይነት ያለው ወደፊት መገንባት

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከ150 ዓመታት በላይ ቆይቷል።ይህ ጊዜ አስቸጋሪ ጊዜ ቢሆንም፣ አዋጭ መፍትሄዎችን መፈለግ መቀጠል አለብን።ይህ ቀጣይነት ያለው የማህበረሰባችን አጋርነት እና ድጋፍ ይጠይቃል።

ይህ አካሄድ የሚቀጥለውን አመት በጀት ለማረጋጋት ይረዳናል።ዘላቂ የሆነ የፊስካል መፍትሄዎችን ለማግኘት በምንሰራበት ጊዜ ይህን ውይይት ከቤተሰቦች፣ከሰራተኞች እና ከትምህርት ቦርድ ጋር ለመቀጠል ቃል ገብቻሎህ። በጋራ፣በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ተማሪ የሚያድግበትን የወደፊት ጊዜ እንፈጥራለን።

ለትምህርት ቤቶቻችን ላደረጋችሁት ቁርጠኝነት እናመሰግናለን።

ከሰላምታ ጋር፣
Dr. Brent Jones
ዋና ሃላፊ
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች